27ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

27ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አብዱላጢፍ ባምባ (መቐለ 70 እንደርታ) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ27ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 88 ኛ ደቂቃ ላይዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል።ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3ዐዐዐ /ሶስት ሺህ/ እንዲከፍል የየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። 2. ጊቢ ጆቤ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) : ክለቡ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ27ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 54 ኛ ደቂቃ ላይኳስ በእጅን በመጫወት የግብ የማግባት አድል በማበላሸት በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት ቀርቦበታል። ስለሆነም ተጨዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 2 አንቀፅ 35(መ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። 3. ተስፋዬ ታምራት (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሀዲያ ሆሳዕና ኢትዮ ኤሌትሪክ -ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ‐ሲዳማ ቡና ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። 4.
ሞይስ ፓዋቲ (ፋሲል ከነማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ፡፡ ፋሲል ከነማ-ሲዳማ ቡና ፋሲል ከነማ-ምድረ ገነት ሽረ ፋሲል ከነማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ‐ፋሲል ከነማ ወላይታ ድቻ-ፋሲል ከነማ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ጌታነህ ከበደ (ሃዋሳ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያካርድ ተመልክቷል ፡፡ ሃዋሳ ከተማ-ነገሌ አርሲ ሃዋሳ ከተማ-ኢትዮ ኤሌትሪክ አዳማ ከተማ-ሃዋሳ ከተማ ሃዋሳ ከተማ-ምድረ ገነት ሽረ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። አሰጋኸኝ ጴጥሮስ (መቐለ 70 እንደርታ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ። ምድረ ገነት ሽረ-መቐለ 70 እንደርታ መቐለ 70 እንደርታ-ሃዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻ-መቐለ 70 እንደርታ መቐለ 70 እንደርታ-ምድረ ገነት ሽረ መቐለ 70 እንደርታ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። 7. በረከት ወልዴ (ነገሌ አርሲ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ። ነገሌ አርሲ አርባምንጭ ከተማ ኢትዮጵያ ቡና-ነገሌ አርሲ ቅዱስ ጊዮርጊስ-ነገሌ አርሲ ነገሌ አርሲ-ኢትዮጵያ መድን ሽገር ከተማ-ነገሌ አርሲ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። አቤኔዘር ህዝቂዬል (ሸገር ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ። ሸገር ከተማ-ሀዲያ ሆሳዕና ሲዳማ ቡና-ሽገር ከተማ መቐለ 70 እንደርታ-ሽገር ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ-ሸገር ከተማ ሸገር ከተማ-ነገሌ አርሲ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡ ስንታየሁ ወለጬ ( ምድረ ገነት ሽረ ) ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል ። ምድረ ገነት ሽረ-ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ምድረ ገነት ሽረ -ባህርዳር ከተማ ኢትዮ ኤሌትሪክ-ምድረ ገነት ሽረ ምድረ ገነት ሽረ -ነገሌ አርሲ ሃዋሳ ከተማ-ምድረ ገነት ሽረ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.አ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ውብሸት ክፍሌ (ወላይታ ድቻ) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድተመልክቷል ። ሃዋሳ ከተማ ወላይታ ድቻ ሲዳማ ቡና-ወላይታ ድቻ ወላይታ ድቻ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻ-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ድቻ ፋሲል ከነማ ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 2 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 35(ሠ) መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 15ዐዐ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ27 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ተጫዋች የሆኑት በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5ዐዐዐ /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡ መቐለ 70 እንደርታ ክለቡ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ባደረገው የ27 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታ ቡድን ተጫዋች የሆኑት በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ሸገር ከተማ ክለቡ ከነገሌ አርሲ ጋር ባደረገው የ27 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሸገር ከተማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት አቤኔዘር ህዝቂዬል በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 65 (ሀ) መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ጊቤ ጆቤ (ተጫዋች-ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) ክለቡ ከሲዳማ ቡና ጋር በነበረው የ27ኛ ሳምንት ግጥሚያ ከሜዳ በቀይ ካርድ ሲወጣ ተመልካቹን በእጅ ምልክት አፀያፍ ሰድብ ስለመሳደቡ ሪፖርት ቀርቦበታል ። ስለሆነም ተጫዋቹ ለፈጸመው ጥፋት ከላይ በተራ ቁጥር 2 ላይ ከተቀጣው በተጨማሪ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሠረት 3 /ሶስት/ ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ ብር 3000 /ሶስት ሺህ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡ ሲዳማ ቡና ክለቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በነበረው የ27ኛ ሳምንት እግር ኳስ ኳስ ግጥሚያ ጨዋታው መጀመር ከነበረበት ሰዓት 21 ደቂቃ ዘግይቱ እንዲጀመር ምክኒያት ስለመሆኑ ሪፖርት ተደርጓል። በመሆኑም ክለቡ ላጠፋው ጥፋት በውድድር ደንብ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ 13.2 ተቁ. 17 መሰረት ብር 25 000/ሀያ አምስት ሺ/ እንዲከፍልየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቡ ከአርባ ምንጭ ከተማ ጋር በነበረው የ27ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በተለምዶ ካታንጋ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የነበሩ የክለቡ ደጋፊዎች 412 ወንበሮችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስለማድረሳቸው ሪፖርት ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ክለቡ ጉዳት የደረሰባቸውን ወንበሮች እንዲያሰራ ወይም ባለንብረቱ አሰርቶ የሚያቀርበውን ዋጋ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡ አርባ ምንጭ ከተማ ክለቡ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በነበረው የ27ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ በግራ ጥላ ፎቅ ቦታ ላይ የነበሩ የክለቡ ደጋፊዎች 10 ወንበሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስለማድረሳቸው ሪፖርት ተደርጓል። በመሆኑም ክለቡ ጉዳት የደረሰባቸውን ወንበሮች እንዲያሰራ ወይም ባለንብረቱ አሰርቶ የሚያቀርበውን ዋጋ እንዲከፍል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል። ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከ ሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው የ27 ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ ወቅት የክለቡ ደጋፊዎች በተለምዶ ሚስማር ተራ በሚባለው ቦታ የነበሩትን 34 ወንበሮች ስለመስበራቸው ሪፖርት ተደርጓል። በመሆኑም ክለቡ የተሰበሩትን ወንበሮች እንዲያሰራ ወይም ባለንብረቱ አሰርቶ የሚያቀርበውን ዋጋ እንዲከፍልየውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡ የመርሀ ግብር ማስተካከያን በተመለከተበአንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 8.1 ተራ ቁጥር 3 በተደነገገው መሰረት ከ28ኛ ሳምንት ጀምሮ የሚደረጉ ጨዋታዎች በማንኛውም ምክኒያት ተጀምረው የሚቋረጡ ወይምመካሄድ የማይችሉ ከሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ጨዋታዎቹ በተከታዩ ቀን የሰዓትና የቦታ ለውጥ ተደርጎ የሚከናወኑ መሆኑን ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ያሳውቃል፡፡